መግቢያ
መግቢያ
አምስቱ ነገሮች
በሕይወት ዘመንዎ ሁሉ እግዚአብሔርን ለማገልገል እና ደስ ለማሰኘት ምን ያደርጋሉ?
ያንን እንዲገነዘቡ ልንረዳዎ እንፈልጋለን! በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 15 ላይ፣ ኢየሱስ የሚኖር ፍሬ ስለማፍራት ተናግሯል። ኢየሱስ እያለ ያለው ፍሬ ምን አይነት ፍሬ ነው? በመንፈሳዊ ህወታቸው ፍሬያማ የሆኑ ሰዎች ለክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ተገዝተው* ደቀ መዛሙርት በማድረግ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ለእርሱ ያላቸውን ፍቅር ይገልጻሉ።
ስኬት የሚጀምረው አሳልፎ በመስጠት ነው።* አብዛኞቹ ክርስቲያኖች ሆን ብለው ከእግዚአብሔር አይሄዱም፤ ነገር ግን ቀስ በቀስ ከእግዚአብሔር ይርቃሉ። ለኢየሱስ ክርስቶስ ይገዛሉ?
እዚህ ጋር እግዚአብሔር ስለ ሰጠዎ ስለ ልዩ ስጦታ እና ተሰጥ ለማሰብ የሚረዱ 5 ነገሮች ተጠቅሰዋል። እነዚህ 5 ነገሮች እራስዎን ትርጉም ባለው መንገድ በማህበረሰብ ውስጥ እንዴት እንደሚሳተፉ እና እግዚአብሔር በሚመራዎት ቦታ ሁሉ እርሱን ለማሳወቅ የሚረዱ ናቸው።
ለእያንዳንዱ ለማሰላሰልና ለመጸለይ ከደብተር ጋር አንድ ሰዓት ያህል መድብ።
ከአምስቱ ነገሮች ውስጥ የመጀመሪያው
1
የመንግስቱ ራዕይ

የክርስቲያን እንቅስቃሴ አካል መሆን ታላቁን ትዕዛዝ (ማቴዎስ 22፡37-39) እና ታላቁን ተልእኮ (ማቴዎስ 28፡18-20) ለመፈጸም ያላችሁን ራዕይ ለመቅረጽ ይረዳል። እንዲሁም አሁን ባለህበት አውድ ውስጥ የእግዚአብሔርን አላማዎች የምትኖርበት እድል ይሰጥሃል። የመንግሥቱ ራዕይ አሁን እና በሚቀጥሉት ዓመታት በውሳኔዎችዎ እና ምርጫዎችዎ ላይ ተጽእኖ በማድረግ ከእግዚአብሔር ትልቁ እቅድ ጋር እንዴት እንደሚያስማሙ ማየት ነው። ሌሎችን በወንጌል ለመድረስ፣ በእምነታቸው እንዲያድጉ በማድረግ እና እነርሱን በመላክ አሁን የምትማረው ነገር ለህይወት ዘመንዎ ፍሬያማነት መሰረት እየጣሉ መሆንዎን ያሳያል። ስለዚህ ዛሬ ዳሰሳ በማድረግ ስለመንግስቱ ያለዎን ራእይ ማሰብ ምን ይመስልዎታል?
ምላሽ
- ምን ዓይነት ፍላጎቶች እና ስጦታዎች አሉዎት? እነዚህን በመጠቀም እግዚአብሔርን ማክበር እና ሌሎችን ማገልገል እንዴት ያያሉ? በግቢ ውስጥ ወይም በማህበረሰብዎ ውስጥ ባሉ የሰዎች ስብስብ ውስጥ ቦታ እና ሸክም አሉዎት?
- ከስጦታዎቾዎ እና ከአገልግሎትዎ ልምድ አንጻር ታላቁን ተልዕኮ እና ታላቁን ትእዛዝ መኖር ምን ይመስሎታል?
- የምትኖሩበት አውድ ስለ መንግስቱ ያሎዎን ራእይ ቅርጽ ያስይዛል። እርስዎ ያሎዎን ራእይ እና ሊሳተፉበት የሚችሉት እንቅስቃሴ፣ ቤተክርስቲያን ወይም ድርጅት አለ?
- እግዚአብሔር ለዚህ ዓላማ ጠርቶኛል ብለው ስለሚያስቡት ጥሪ አጭር መግለጫ ይጻፉ።
ከአምስቱ ነገሮች ውስጥ ሁለተኛው
2
ቡድን

ብቻህን አትሂድ። ያለቡድን ሰዎች ለጥቂት ጊዜ ሊሄዱ ይችላሉ። መክብብ ምዕራፍ 4፡9 እንዲህ ይላል። “ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል”… አንዱ ቢወድቅ ሌላው ይረዳል። ሌሎች ለኢየሱስ ከተገዙት፣ ከተሰጡት እና ተመሳሳይ የመንግስት ራዕይን ጋር ይቀላቀሉ ስራዎንም ያካፍሉ። በስብሰባ ብቻ ወንበር አያሞቁ፡ ከጓደኞችዎ ጋር በሚስዮናዊነት ይኑሩ። ከሰዎች ጋር ለመጸለይ፣ ለማቀድ፣ ለመበረታታት እና ያንን ራዕይ በጋራ ለመኖር ይሰብስቡ።
ምላሽ
- በእንቅስቃሴዎ ወይም በቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀድሞ የእርስዎን ራዕይ የሚከታተል ቡድን አለ? ልትቀላቀልባቸው ትችላለህ?
- ካልሆነ፣ ለኢየሱስ ህይወቱን የሰጠ እና ተመሳሳይ የመንግሥቱ ራእይ ያለው ማንን ያውቃሉ?
- ጥሪዎን ለመኖር ከእርሶ ጋር ሊተባበሩ የሚችሉ ቢያንስ ሁለት ሰዎችን ያስቡ።
- ለመጸለይ፣ ለማቀድ እና በትክክል በተልዕኮ ለመኖር ከቡድንዎ ጋር መቼ መገናኘት ይችላሉ?
ከአምስቱ ነገሮች ውስጥ ሦስተኛው
3
እቅድ

ምንም ዓላማ ከሌለህ፣ ምንም አታሳካም። እግዚአብሔር የሰጠህን ራዕይ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዱ ቀላል እና ሊደረጉ የሚችሉ እቅዶች ያስፈልግዎታል። የተብራራ መሆን የለበትም፣ መጨረሻውን ግምት ውስጥ በማስገባት ያቅዱ። እቅድ፣ የመንግስቱን ራዕይ ለማሳካት በትኩረት የሚወሰዱ እርምጃዎች ናቸው።
ምላሽ
- ቡድንህ ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኝበት ጊዜ፣ ምን የተለየ የእምነት እርምጃ እንድትወስድ እየጠየቀህ ነው?
- በህይወትህ ውስጥ እግዚአብሔር ባንተ ውስጥ ካስቀመጠው የመንግስቱ ራእይ አንጻር ልወስዱ የሚችሉት ሶስት እርምጃዎች ምንድናቸው?
ከአምስቱ ነገሮች ውስጥ አራተኛው
4
ተከታታይ ስልጠና

ስኬታማ ሰዎች ሁልጊዜ የሚያድጉ ናቸው። ውጤታማ ድርጅቶች ሁልጊዜ አዲስ ነገር ለመልመድ ዝግጁ የሆኑት ናቸው። ቀጣይነት ያለው ስልጠና የመንግሥቱን ራዕይ እንድትኖር የሚያግዙህ ናቸው። ይህ ተጨማሪ ትምህርትን መማር፣ ክህሎቶችን፣ መሳሪያዎችን፣ ስልጠናዎችን እና ግብዓቶችን ሊያካትት ይችላል። እነዚህ ነገሮች ከእግዚአብሔር ጋር ለመራመድ እና በሕይወት ዘመናችሁ እርሱን ለማገልገል በምትጓዙበት ጉዞ ውስጥ ይረዱዎታል።
ምላሽ
- “ጥሪዬን በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት የትኞቹን የሕይወቴ ዘርፎች ማዳበር አለብኝ?” በማለት ራስህን ጠይቅ።
- ለመንግሥቱ ሥራ እርስዎን ለማስታጠቅ የሚረዱ ምን መጽሐፍ ማንበብ ይችላሉ? ለዚህ ዓላማ የሚያግዙ ኮንፈረንሶች ወይም ሌሎች የስልጠናዎች አሉ?
- አሁን፣ የመንግስቱን ራዕይ ለማሳካት እራስዎን በተሻለ ሁኔታ ለማብቃት ምን ሶስት ነገሮች ያደርጋሉ?
ከአምስቱ ነገሮች ውስጥ አምስተኛው
5
አሠልጣኝ

መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ጥበብ የማግኘትን አስፈላጊነት ያጎላል (ምሳሌ 16፥16)። ከእኛ በፊት የሄደና በመንገዱ አንድ ሁለት ነገር የተማረ ሰው የሚሰጠውን በረከት በፍጹም ማቃለል የለብንም። አሰልጣኝ ማለት ልክ እንደዚያ ሰው ነው፦ ጥያቄዎችህን የሚመልስ፣ አንተና ቡድንህ ስትታገዱ የሚረዳ፣ ነገሮች ሲከብዱም የሚያበረታታ።
ምላሽ
- እርሶ ያሎዎን ራዕይ ቀድሞ የኖረ ሰው ማን ነው? ከእነሱ ምን ይማራሉ?
- የእርሶ አመካሪ እና ራዕይዎን ለማሳካት የሚረዳዎት ሰው ማን ነው? ከለሉት ማን ልሆን ይችላል?
አሁን ምን
አሁን ምን
ስለዚህ አሁን ስለ 5 ነገሮች ግንዛቤ አለዎት፤ ነገር ግን ከላይ ያሉትን ሁሉንም ጥያቄዎች ላይመልሱ ይችላሉ? ከማን ጋር መተባበር እንደሚችሉ ወይም እንዴት መጀመር እንደሚችሉ እርግጠኛ ካልሆኑስ?
ይጸልዩ
እግዚአብሔር “አስቀድመው ወዳዘጋጀው መልካም ስራ” ለመስራት ይለምኑ (ኤፌ. 2፡10)። እንዲመራዎ እና እርሶ በተልእኮ እንድኖሩ የሚያስፈልጎዎን ነገሮች እንዲያቀርብሎዎት ይጠይቁ።
ይዘጋጁ
ከርሶ አማካሪ፣ አብሮ ሰራተኛ እና ተመሳሳይ ራእይ ካሉት ጋር ይገናኙ። ከመመረቅዎ ወይም አሁን ያሉበትን ሰራ ከመልቀቅዎ በፊት እናዚህን 5 ነገሮች እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችሉ እቅድ ያውጡ።
ይጠይቁ
እንደ እርስዎ ተመሳሳይ የመንግስቱን ራዕይ የሚጋሩ ሌሎችን ለማግኘት ይጠይቁ።
እርምጃ ውሰድ
ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው ደቀመዛሙርት ጋር ለመጸለይ፣ ለማቀድ እና አንድ ላይ ተልእኮውን ለመፈጸም፣ እርስ በርስ ለመበረታታት በመደበኛነት መገናኘት ይጀምሩ።
እነዚህን 5 ነገሮች በህይወትዎ ላይ መተግበር በእርግጠኝነት ጊዜ የሚጠይቅ ነው። ነገር ግን ለክርስቶስ ከተገዙ እና እነዚህን ነገሮች ተግባራዊ ካደረጉ፣ አሁን እና በመጪዎቹ አመታት ጉልህ ተጽእኖ ደርጋሉ።
